Fana: At a Speed of Life!

ለአንድ ወር የሚቆይ የመጻሕፍት የማሰባሰብ መርሐ ግብር ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “ሚሊየን መጻሕፍት ለሚሊኒየሙ ትውልድ” በሚል መሪ ቃል ለአንድ ወር የሚቆይ የመጻሕፍት ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር  በይፋ ተጀመረ፡፡

ለአብርሆት ቤተ መጻሕፍት÷ መጻሕፍት ለማሟላት ያለመ ከሚያዝያ 28 እስከ ግንቦት 29 የሚቆይ የመጻሕፍት ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ዛሬ በይፋ ተጀምሯል።

ኢትዮጵያ ቤተ መጻሕፍትን በማቋቋም ከ75 ዓመት በላይ የቆየ ልምድ ቢኖራትም ይህህኑ ልምድ ማስቀጠል ሳይቻል መቅረቱ ተመላክቷል፡፡

አሁን ይህንን ታሪክ ለመቀየርና አንባቢ ትውልድ ለመፍጠር በአብርሆት ቤተ መጻሕፍት÷ መጻሕፍትን የማሰባሰብ ስራ መጀመሩን ገልጿል።

የአብርሆት ቤተ መጻሕፍት ከግንባታው መጠናቀቅ በኋላ በመጻሕፍት የመሙላት ስራ የሚጠይቅ በመሆኑ÷ በየግለሰቦች እጅ ላይ የሚገኙ ህትመታቸው የቆሙ እና ገበያ ላይ የማይገኙ መጻሕፍትን ለማግኘት እንዲቻል ከግዥ ይልቅ ከማህበረሰቡ ማሰባሰብ አስላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

በተጨማሪም በአጭር ጊዜ በርካታ መጻሕፍትን ለማግኘት የሚረዳ መሆኑም ተመላክቷል፡፡

4 ሚሊየን መጻሕፍት የመያዝ አቅም ያለው ቤተ መጻሕፍቱ÷ በዚህ ወር ብቻ አንድ ሚሊየን መጻሕፍትን በማሰባሰብ ገቢ የሚደረግ ሲሆን ወደ ሌሎች ክልሎችም ድጋፍ የማድረግ ስራ ይሰራል ተብሏል።

ይህንን መርሐ ግብር የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት፣ የአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ፣ የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ፣ የኢትዮጵያ ደራሲያን ማኅበር እና አብርሆት ቤተ መጻሕፍትን እያስተዳደረ የሚገኘው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በበላይነት  ይመሩታል።

 

በዘመን በየነ

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.