Fana: At a Speed of Life!

3ኛው ዙር የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ተጠናቀቀ

 

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዳማ ከተማ ሲካሄድ የቆየው 3ኛው ዙር የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ተጠናቋል፡፡

3ኛው ዙር መርሐ ግብር ትናንት ምሽት ፋሲል ከነማ ወላይታ ዲቻን 3 ለ 1 በረታበት ጨዋታ ነው መቋጫውን ያገኘው፡፡

በ3ኛው ዙር የአዳማ ቆይታ በአጠቃላይ 48 ጨዋታዎች ተከናውነው 110 ጎሎች የተቆጠሩ ሲሆን÷ ሃዲያ ሆሳዕና እና ቅዱስጊዮርጊስ በአዳማ ቆይታቸው ያልተረቱ ቡድኖች በመሆን መርሐ ግብሩን ማጠናቀቅ ችለዋል፡፡

ፋሲል ከነማ በአዳማ በነበረው ቆይታ ከነበረበት የውጤት ቀውስ በመውጣት 2ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠ ሲሆን÷ በባሕርዳር በሚካሄደው 4ኛው ዙር የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስን ይፈትነዋል ተብሎ ይጠበቃል።

ሰበታ ከተማ፣ ጅማ አባ ጅፋር እና አዲስ አበባ ከተማ በአዳማ ቆይታቸው ወራጅ ቀጠና ውስጥ የተቀመጡ ቡድኖች ሆነዋል፡፡

የከፍተኛ ጎል አስቆጣሪነት ደረጃውን ኢስማኤል አጉሮ ከቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሪችሞንድ አዶንጎ ከአዲስ አበባ ከተማ በእኩል 10 ጎል ሲመሩ÷ ይገዙ ቦጋለ ከሲዳማ ቡና እና ጌታነህ ከበደ ከወልቂጤ ከነማ በእኩል 9 ጎል ይከተላሉ፡፡

የ22ኛው ሣምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በባሕር ዳር የሚደረግ ሲሆን÷ በሣምንቱ መጨረሻ በሚደረጉ ጨዋታዎች ጅማሮውን ያደርጋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.