Fana: At a Speed of Life!

ከምርታማነት ውጭ ብልፅግናን ማሳካት አይታሰብም- አቶ መላኩ አለበል

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከምርታማነት ውጭ ብልፅግናን ማሳካት አይታሰብም ሲሉ የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ተናገሩ፡፡
አቶ መላኩ አለበል የ”ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄን አስመልክተው ዛሬ በሰጡት መግለጫ፥ ንቅናቄው የአምራች ኢንዱስትሪውን ማነቆ መፍታት፣ ለዘላቂ ልማትና ተወዳደሪነት ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ያለመ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የንቅናቄው ሀገር አቀፍ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በመጭው ሚያዝያ 29 እንደሚካሄድ ጠቁመው፥ እስካከሁን በተለያዩ ክልሎች ሲካሄድ መቆየቱንም አስታውሰዋል፡፡
የእስካሁን የንቅናቄው አካል የሆኑ ውይይቶችና መርሐ ግብሮች የዘርፉን ችግሮች ማወቅ ያስቻሉ፣ ማምረት ያቆሙ አምራቾችን ወደ ምርት የመለሱ፣ ምርታማነትን ለማሳደግ ተጨማሪ ጉልበት የሚሆን እና አዳዲስ ኢንቨስትመንቶችም እንዲፈጠሩ አስችለዋል ብለዋል፡፡
በዚህም፥ ሥራ ካቆሙት 446 አምራቾች 118 የሚሆኑት ወደ ምርት መመለሳቸውን ለአብነት አንስተዋል፡፡
በአማካይ ከማምረት አቅማቸው 50 በመቶውን ብቻ የሚጠቀሙ ኢንዱስትሪዎች ባሉበት ሁኔታ እድገት የማይታሰብ በመሆኑ÷ ችግሮቹን ፈትቶ ለስራ እድልና ለጠቅላላ ገቢ ምርታማነትን ማሳደግ ወሳኝ በመሆኑ ንቅናቄው ማስፈለጉን አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
በ2022 ኢትዮጵያ ለማሳካት የያዘቻቸውን እቅዶች እንዲሳኩም ያግዛል ነው ያሉት፡፡
እስካሁን በተካሄዱ ውይይቶች፥ የግብአት አቅርቦት፣ የፋይናንስ ችግር፣ የመሰረተልማት አቅርቦት ችግር፣ የሰለጠነ የሰው ኃይል እጥረት እና የተቀናጀ ድጋፍ ከመንግስት አለማግኘት የሚሉት ዋና ዋና ችግሮች ተብለው መለየታቸውንም በመግለጫቸው አመላክተዋል፡፡
በሀብታሙ ተክለ ስላሴ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.