አዲስ አበባ ከተማ የእግር ኳስ ቡድን ለሁለተኛ ጊዜ አሰልጣኙን አሰናበተ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሊጉ ወራጅ ቀጠና ላይ የሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ እግርኳስ ቡድን በ6 ወር ውስጥ ሁለተኛውን አሰልጣኝ ደምሰው ፈቃዱን አሰናብቷል፡፡
በአስተዳደራዊ ጉዳዮች ምክንያት ችግር ውስጥ የገባው የአዲስ አበባ ከተማ እግርኳስ ቡድን÷ በ21 ነጥብ ወራጅ ቀጠና ውስጥይገኛል፡፡
በዛሬው ዕለት 4ኛ ዙር ውድድሩን ለማድረግ ወደ ባሕር ዳር ያቀናው ቡድኑ÷ የአሰልጣኝ ደምሰው ፈቃዱን መሰናበት ተከትሎ በቅርቡ አዲስ አሰልጣኝ እንደሚቀጥር ይጠበቃል፡፡
አዲስ አበባ ከተማ ቀደም ሲል አሰልጣኝ እስማኤል አቡበከርን ማሰናበቱ ይታወሳል፡፡