የሰብዓዊ ድጋፍ የያዙ 16 የጭነት ተሽከርካሪዎች መቀሌ ገቡ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰብዓዊ ድጋፍ የያዙ 16 ተጨማሪ የጭነት ተሽከርካሪዎች በዚህ ሳምንት መቀሌ መግባታቸውን የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስታወቀ፡፡
በያዝነው ሣምንት መቀሌ ከደረሱት የሰብዓዊ ድጋፍ የጫኑ 16 ተሽከርካሪዎች በተጨማሪ÷ 64 ሌሎች ተሽከርካሪዎች በጉዞ ላይ መሆናቸውንም አመላክቷል፡፡
ባሳለፍነው ሚያዝያ ወር በሽራሮ አካባቢ ለሚገኙ 45 ሺህ ሰዎች ምግብ ማድረስ እንደተቻለ እና ለ11 ሺህ ሴቶች እና ሕጻናት አልሚ ምግብ ማሰራጨቱን አመላክቷል፡፡
ሰብዓዊ ድጋፍ ለሚሹ ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ተጨማሪ ድጋፍ ለማድረግ በማጓጓዝ ላይ መሆኑንም ነው የዓለም ምግብ ፕሮግራም ያስታወቀው፡፡