Fana: At a Speed of Life!

ሃሰተኛ የአሜሪካ ዶላር ሲመነዝሩ የተገኙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 29 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሃሰተኛ የአሜሪካ ዶላር በመጠቀም በኢትዮጵያ ብር ሲመነዝሩ የተገኙ 3 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ ።

ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት ትናንት በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ልዩ ቦታው ዲ አፍሪክ ሆቴል አካባቢ ነው ።

የልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ሃሰተኛ የአሜሪካ ዶላር ይዘው በብር ለመመንዘር የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች ስለመኖራቸው ከህዝብ በደረሰው ጥቆማ እና ባደረገው ክትትል ተጠርጣሪዎቹ ዶላር ከሚፈልጉ ሰዎች ጋር ተቀጣጥረው በተሽከርካሪ ወደ ዲ-አፍሪክ ሆቴል በመምጣት አንዱን ሃሰተኛ ባለመቶ የአሜሪካ ዶላር በ62 ብር ሲመነዝሩ ተገኝተው እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል፡፡

በወቅቱም 97 ባለ መቶ ሃሰተኛ የአሜሪካ ዶላር እና በዶላሩ ልክ የተቆራረጡ ወረቀቶች ይዘው መገኘታቸውን የጠቀሰው የአዲስ አበባ ፖሊስ በተጠርጣሪዎቹ ላይ ምርመራ እየተደረገ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡

ህብረተሰቡ እንደዚህ አይነት ወንጀሎች እንዳይፈፀሙ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ከማድረግ ጎን ለጎን መረጃ የመስጠት ድጋፍ እና ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪውን አቅርቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.