Fana: At a Speed of Life!

“አዲስ አበባ የሰላምና የአብሮነት ከተማ” በሚል መሪ ሀሳብ ሕብረተሰብ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ አበባ የሰላምና የአብሮነት ከተማ በሚል መሪ ሃሳብ ሕብረተሰብ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በጋራ ተካሄደ።
በሕብረተሰብ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴው ላይ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ ስፖርተኞች፣ ተማሪዎች ወጣት ሴቶችና ወንዶች ተገኝተው በጋራ መካሄዱን ከከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት÷ አዲስ አበባ የሰላም፣ የፍቅር፣ የአብሮነትና የኢትዮጵያዊነት መገለጫ ከተማ ናት፡፡
ሁላችንም በጋራ በያለንበት አካባቢ የሕብረተሰብ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ልማድ በማድረግ አንድነታችንን ልናጠናክር ይገባል ብለዋል ፡፡
ለአብሮነታችን እና ለፍቅራችን እንጂ ለጥላቻ ጊዜ የለንም ያሉት ከንቲባ አዳነች፥ የግጭት ነጋዴዎች በፍፁም አዲስ አበባ ላይ ሊፈነጩ አይችሉም ሲሉም ተናግረዋል፡፡
አዲስ አበባ ለየትኛውም የኢትዮጵያ ክፍል የአብሮነት ምሳሌ ናት ያሉት ከንቲባዋ፥ ህዝቦቿ በፍቅር ያለምንም ልዩነት አብሮ በመኖር ምሳሌ መሆናቸውንም አንስተዋል፡፡
ሕብረተሰብ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን አዘውትረን ከመስራታችን ጎን ለጎን የመለያየት ነጋዴዎችን የግጭት ጠማቂዎችን እምቢ ልንላቸው ይገባል ይህም የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ሃላፊነት ነው ሲሉም አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.