Fana: At a Speed of Life!

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከተለያዩ አካላት ያሰባሰበውን ድጋፍ ለተፈናቃይ ወገኖች አስረከበ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከሠራተኞችና ከለጋሾች ያሰባሰበውን 8 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የአልባሳት እና የምግብ አቅርቦት ድጋፍ በአፋር ክልል ለሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖች አስረክቧል፡፡
የክልሉ አደጋ መከላከልና ዝግጁነት ኮሚሽን ኃላፊ አቶ መሐመድ ሁሴን ተፈናቃዮቹ ከበራህሌ፣ ኮነባ፣ አብአላ፣ ኢረብቱ እና ዳሉል ወረዳዎች መምጣታቸውን ገልጸው÷ ተፈናቃዮቹን ወደ ቀያቸው ለመመለስ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ተፈናቃዮቹ ወደ ቀያቸው እስከሚመለሱ እና ሄደው እንዲቋቋሙ ተጨማሪ ድጋፍ እንደሚያስፈልግም ኃላፊው አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
በዱብቲ በጊዜያዊነት ተጠልለው የሚገኙ ተፈናቃዮች ችግር ከክልሉ አቅም በላይ በመሆኑ የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት ሊሰጡት እንደሚገባም ተመላክቷል፡፡
በጊዜያዊ መጠለያው እስከ 300 ሺህ የሚደርሱ ተፈናቃይ ወገኖች እንዳሉ እና የዕለት ፍጆታ የሚውል የምግብ አቅርቦት እጥረት መኖሩም ተገልጿል፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሴቶችና ሕጻናት ጉዳዮች ዳይሬክተር ወይዘሮ ኤልሳቤጥ ገብረ ስላሴ፥ ለሚመለከታቸው አካላት ጥያቄውን እንደሚያቀርቡ መናገራቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.