Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ካራቴ ሻምፒዮና በአማራ ክልል አጠቃላይ አሸናፊነት ተጠናቀቀ

 

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአርባ ምንጭ ከተማ  ሲካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ ካራቴ ሻምፒዮና በአማራ ክልል የበላይነት ተጠናቋል።

በሻምፒዮናው የተሳተፈው የአማራ ክልል የካራቴ ስፖርት ልዑካን ቡድን÷ 6 ወርቅ 7 ብር እና 3 ነሃስ ሜዳሊያ በመሰብሰብ አንደኛ ሆኖ አጠናቋል፡፡

ድሬደዋ ከተማ በ5 ወርቅ 4 ብርና 4 ነሃስ ሁለተኛ  ሲሆን የኦሮሚያ ክልል ደግሞ በ2 ወርቅ 3 ብርና 8 ነሃስ ሜዳሊያ ሶስተኛ ሆነው አጠናቀዋል፡፡

በፍፃሜው ዕለት በተደረገ የወንዶች  እና የሴቶች ኩምቴ አማራ ክልል የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ሆኗል፡፡

በአጠቃላይ አማራ ክልል አራት ዋንጫዎችን በመሰብሰብ የ2014 ዓ.ም የኢትዮጵያ ካራቴ ሸምፒዮና በመሆን ውድድሩን ማጠናቀቁን ከክልሉ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

አማራ ክልል በ2013 ዓ.ም በደሴ ከተማ በተካሄደው የኢትዮጵያ ካራቴ ሻምፒዮና መሆኑ ይታወሳል ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.