Fana: At a Speed of Life!

የሸዋል ኢድ በዓል አንድነትንና ፍቅርን በሚያጠናክር መልኩ ማክበራቸውን የበዓሉ ተሳታፊዎች ተናገሩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል በድምቀት የተከበረው የሸዋል ኢድ በዓል አንድነትንና ፍቅርን በሚያጠናክር መልኩ መከበሩን የበዓሉ ተሳታፊዎች ተናግረዋል።
የዘንድሮ የሸዋል ኢድ በዓል ከሐረሪ ብሔረሰብ በተጨማሪ ሁሉም የክልሉ ብሔር ብሔረሰብን ባሳተፈ መልኩ በድምቀት መከበሩን ጠቁመው÷ ይህም አንድነትን፣ ሰላምንና አብሮነትን ከማጠናከር አንፃር ጉልህ ሚና እንዳለው ተናግረዋል፡፡
በተለይ የዘንድሮው የበዓል አከባበር ሸዋል ኢድን በዩኔስኮ ለማስመዝገብ የሚደረገውን ጥረት እንደሚያግዝ ገልጸው÷ የክልሉ መንግስትም በዓሉን በአለም ቅርስነት እንዲመዘገብ እያደረገ የሚገኘውን ጥረት አጠናሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡
በዓሉ እርስ በእርስ እንድንተዋወቅና ምቹ ሁኔታን የፈጠረ ከመሆኑም በተጨማሪ÷ ባህልን ከማሳደግ አንፃር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት መናገራቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.