በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ፋሲል ከነማ ሲዳማ ቡናን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ23ኛ ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ፋሲል ከነማ ሲዳማ ቡናን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡
የፋሲል ከነማን የአሽናፊነት ጎል ፈቃዱ አለሙ በ75ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል፡፡
አጼዎቹ ዛሬ ማሸነፋቸውን ተከትሎ ነጥባቸውን 40 በማድረስ 2ተኛ ደረጃን አስጠብቀዋል፡፡
10 ሰአት ላይ በተካሄደ ጨዋታ ደግሞ ወልቂጤ ከተማ ከአዲስ አበባ ከተማ አንድ አቻ ተለያይተዋል።