Fana: At a Speed of Life!

የጋምቤላ ክልል የመንግስት የስራ ሰዓት ከዛሬ ጀምሮ ወደ ቀድሞው ተቀይሯል – የክልሉ መንግስት

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል የሙቀት መጠኑ እየቀነሰ መምጣቱን ተከትሎ የመንግስት የስራ ሰዓት ወደ መደበኛ የስራ ሰዓት መቀየሩን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።
የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ፒተር ሆው የሙቀት መጠኑ ቀንሶ ለስራ ምቹ መሆኑን ጠቅሰው÷ ባለፉት 3 ወራት ከጠዋቱ 1 ሰዓት እስከ 5 ሰዓት ከ 30 የነበረው ከ1 ሰዓት እስከ 6 ሰዓት ከ30 እንዲሁም ከሰዓት በኋላ ከ10 ሰዓት እስከ 12 ሰዓት ከ30 የነበረው ከ9 ሰዓት እስከ 11 ሰዓት ከ30 ሆኖ በቀድሞው የመደበኛ የስራ ሰዓት መቀየሩን አስታውቀዋል፡፡
የክልሉ የመንግስት ሰራተኞች በተጠቀሰው ጊዜ ወደ ቢሮ በመግባት የተለመደ ሥራቸውን እንዲያከናውኑም አሳስበዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት የጋምቤላ ክልል የሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት ማዕከል ጊዜያዊ ዳይሬክተር አቶ ተስፋሁን ዓለሙ ÷ የክልሉ አማካይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን 31 ዲግሪ ሴልሺስ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የሌሊቱ የሙቀት መጠን ደግሞ 17 ዲግሬ ሼልሲየስ መድረሱን ጠቁመው÷ ባለፉት ሶስት ወራት የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን 42 ነጥብ 5 የሌሊቱ ደግሞ 26 ዲግሪ ሼልሲየስ ደርሶ እንደነበር መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.