Fana: At a Speed of Life!

ሚኒስቴሩ የቆላማ አከባቢ የኑሮ ማቋቋሚያ ፕሮጀክቶች ላይ ከፑንት ላንድ እና ከሶማሊያ ልዑካን ቡድኖች ጋር የልምድ ልውውጥ እያደረገ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስቴር እያከናወናቸው ባሉ የቆላማ አከባቢ የኑሮ ማቋቋሚያ ፕሮጀክቶች ላይ ከፑንት ላንድ እና ከሶማሊያ ከመጡ ልዑካን ቡድኖች ጋር የልምድ ልውውጥ እያደረገ ነው።
በልምድ ልውውጡ በቆላማ አከባቢዎች ላይ እየተከናወኑ ስላሉ ተግባራት ከነገ ጀምሮ የልዑካን ቡድኖቹ ጉብኝት እንደሚያደርጉም ነው የተገለጸው።
በዚህ መርሃ ግብር ላይ ንግግር ያደረጉት የመስኖና ቆላማ አከባቢዎች ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሃመድ÷ ኢትዮጵያ፣ ሶማሊያ እና ፑንት ላንድ በፖለቲካው መስክ ብቻ ሳይህን በእንዲህ ዓይነቱ ማህበራዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ጉዳዮች ላይም ልምዳቸውን ሊለዋወጡ ይግባል ብለዋል።
የልምድ ልውውጡ የሙያ ብቻ ሳይሆን ሁለቱም ወገኖች ያላቸውን ተመሳሳይ የተፈጥሮ ሃብት በምን መንገድ ማልማት እንድሚችሉም እውቀት የሚገኝበት እንደሆነም በመርሃ ግብሩ መክፈቻ ላይ ተመላክቷል።
በይስማው አደራው
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.