Fana: At a Speed of Life!

ጉግል በቋንቋ መተርጎሚያ አገልግሎቱ ውስጥ ኦሮምኛ እና ትግርኛን አካተተ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጉግል ኩባንያ በቋንቋ መተርጎሚያ አገልግሎቱ ዝርዝር ውስጥ የኦሮምኛ እና ትግርኛ ቋንቋዎችን አካተተ።

ኩባንያው ከ300 ሚሊየን በላይ በሆኑ ሰዎች የሚነገሩ በአጠቃላይ 24 አዳዲስ ቋንቋዎችን ወደ መተርጎሚያ ዝርዝር ውስጥ ማካተቱ ታውቋል።

ከነዚህም ውስጥ አስር ተጨማሪ የአፍሪካ ቋንቋዎችን እንዳካተተ የተገለጸ ሲሆን፥ ኦሮምኛ እና ትግርኛ ቋንቋዎችም ተካተውበታል፡፡

ባምባራ በማሊ የሚነገር ቋንቋን ጨምሮ ኢው በጋና እና በቶጎ፣ ክራዮ በሴራሊዮን ሊንጋላ ኮንጎን ጨምሮ በመካከለኛው አፍሪካ ፣ ሉጋንዳ በኡጋንዳ እና በሩዋንዳ፣ ሰፐዲ እና ሶንጋ በደቡብ አፍሪካ እንዲሁም በጋና የሚነገር የትዊ ቋንቋ በጉግል የትርጉም አገልግሎት መሰጠት የጀመሩ የአፍሪካ ቋንቋዎች ናቸው፡፡

ቀደም ባሉት ጊዜያት “ጉግል ትራንስሌት” ለመተርጎም እና ቀድሞውኑ የተተረጎመውን ይዘት ትርጉሙን እንዴት ማሻሻል እንደሚቻል ይረዳል።

በስፋት በሚነገሩ ቋንቋዎች ትልቅ እና እያደገ ያለ የጽሑፍ ስርዓት ያለ ቢሆንም ሁሉም ቋንቋዎች ላይ ግን እንደማይታይ ነው የተገለጸው።

ጉግል እነዚህ አዳዲስ ተጨማሪ ቋንቋዎች ትርጉማቸው የቀድሞ ምሳሌዎችን በማያጣቅሱ አዳዲስ ሶፍትዌሮች ላይ የተመሰረቱ ናቸው ብሏል።

ጉግል መተርጎሚያ ተመራማሪ አይዛክ ካስዌል ለቢቢሲ እንደተናገሩት፥ ይህ ስራ በጎግል ብቻ ሳይሆን በሌሎች ቴክኖሎጂዎች ለሌሎች ማህበረሰቦች ሽፋንን የማስፋት ተግባር አንድ አካል ነው ብለዋል።

ጉግል መተርጎሚያ ብዙውን ጊዜ የቋንቋውን ረቂቅነት እንዲሁም ውስብስብነት ያጣል ከሚሉ ወገኖች መካከል የጉግል ትራንስሌት ተመራማሪ ይዛክ ካስዌል አንዱ ናቸው።

ያም ሆኖ በእነዚህ ቋንቋዎች የትርጉም አገልግሎቱ መጀመሩ አወንታዊ መሆኑን ተመራማሪው አንስተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.