የዓለም የምግብ ፕሮግራም በትግራይ ክልል 3 ሺህ ቶን ምግብ ማከፋፈሉን አስታወቀ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም የምግብ ፕሮግራም ባለፈው ሳምንት የእርዳታ አቅርቦት የጫኑ 165 ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ ክልል ደርሰው 3 ሺህ ቶን ምግብ ማከፋፈሉን ይፋ አደረገ፡፡
የምግብ አቅርቦቱ ለ120 ሺህ ዜጎች ተደራሽ መሆኑን የዓለም የምግብ ፕሮግራም ገልጿል፡፡
በአሁኑ ወቅትም እርዳታ የጫኑ 94 ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ እያቀኑ መሆኑንም አስታውቋል።
በአፋር እና በአማራ ክልልም የምግብ እርዳታ ለማሰራጨት በሂደት ላይ ነው ማለቱን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።