Fana: At a Speed of Life!

የድሬ ዳዋ ከተማ አስተዳደር በግንባታ ላይ የሚገኙ ፕሮጀክቶች በፍጥነት እንዲጠናቀቁ አሳሰበ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬ ዳዋ ከተማ አስተዳደር በግንባታ ላይ ያሉ አዳዲስ እና ነባር ፕሮጀክቶች 2014 ዓ.ም ከመጠናቀቁ በፊት እንዲጠናቀቁ አሳሰበ፡፡
የአስተዳደሩ ከንቲባ አቶ ከድር ጆሀር በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንደገለጹት÷ “በአስተዳደራችን ከሚከናወኑ ነባርና አዳዲስ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች ውስጥ አብዛኛዎቹ በሚያሳዝን ሁኔታ መጓተታቸውን በግምገማ ለይተናል“ ብለዋል፡፡
ለፕሮጀክቶቹ መጓተት በዋናነት የግንባታ ተቋራጮች እና ባለድርሻ አካላት በየደረጃው አስተዋፅኦ እንዳላቸው ከንቲባ ከድር አንስተዋል፡፡
አስተዳደሩ በድሬዳዋ ህዝብ የሚቀልዱ አካላትን ከዚህ በላይ እንደማይታገስ እና በሌሎች የግንባታ ስራዎችም እንደማያሳትፍ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
አክለውም ከያዝነው በጀት ዓመት መጠናቀቅ አስቀድሞ ሁሉም ተቋራጮች የጀመሩትን ግንባታ በተገቢው ጥራት አጠናቀው እንዲያስረክቡ ጥብቅ ትዕዛዝ ተላልፏል ብለዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.