በደቡብ ወሎ ዞን በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 7 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ወሎ ዞን በቦረና ወረዳ ቀበሌ19 በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡
አደጋው የደረሰው ዛሬ ከቀኑ 2ሰዓት ከመካነ-ሠላም ወደ መርጦለማሪያም 26 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረው አነስተኛ የህዝብ ማመላለሻ መኪና በመገልበጡ መሆኑን የቦረና ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡
በዚህም አሽከርካሪውን ጨምሮ የ6 ሠዎች ህይወት ሲያልፍ 9 ተሳፋሪዎች ላይ ከባድ እንዲሁም 11 ተሳፋሪዎች ላይ ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱ ታውቋል፡፡
የወረዳው ፖሊስ ጽህፈት ቤት ንዑስ ክፍል ቁጥጥርና ክትትል የስራ ሂደት ሀላፊ ሳጅን ይርጋ ጀማል እንደገለፁት÷ ተሸከርካሪው ከአቅም በላይ መጫኑና 75 ሜትር የሚሆን ገደል ውስጥ መግባቱን መግለፃቸውን ከቦረና ወረዳ የመንግስት ኮሙንኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡