ሀገርን የሚያፈርሱ አጀንዳዎችን መመከት የሚቻለው አንድነትን ማጠናከር ሲቻል ነው – ምሁራን
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከውስጥ እና ከውጭ ኃይሎች የሚቀርቡ ሀገርን የሚያፈርሱ አጀንዳዎችን መመከት እና መከላከል የሚቻለው ሀገራዊ አንድነትን ማጠናከር ሲቻል ነው ሲሉ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁራን ተናገሩ፡፡
ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት ምሁራን÷ ከውስጥ እና ከውጭ የሚቀርቡ አጀንዳዎች ሰላምን በማደፍረስ በኩል ሚናቸው የጎላ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካ አስተዳደር እና ልማት ተመራማሪ ዶክተር መሀመድ አሊ÷ ኢትዮጵያውያን አንድ የሚያደርጋቸው እሴቶች ስላላቸው ነው የመበታተን አጀንዳን እያከሸፉ ያሉት ብለዋል።
በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር ዶክተር ቃለወንጌል ምናለ÷ ለሀገር አንድነት እና ሰላም ፀር የሆኑ አጀንዳዎችን የሚያከሽፉ ትክክለኛ መረጃዎችን ለህብረተሰቡ ማድረስ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያውያን የውስጣቸውን ጉዳይ በንግግር መፍታት ተስኗቸው ከፈረሱ ሀገሮች ታሪክ መማር ይኖርባቸዋል ብለዋል ምሁራኑ፡፡
በአልማዝ መኮንን