Fana: At a Speed of Life!

በቱርክ አዳና ግዛት የሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎች በኢትዮጵያ መዋዕለ ነዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ሃላፊዎችን ያካተተው የኢንቨስትመንት እና ፕሮሞሽን ልዑካን ቡድን በቱርክ የሚገኘውን አዳና ግዛት ጎብኝቷል፡፡

የልዑካን ቡድኑ በግዛቱ የሚገኘውን አዳና ሃቺ ሳባንቺ የተደራጀ የኢንዱስትሪ ዞንን የጎበኘ ሲሆን÷ በዞኑ የሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎች በኢትዮጵያ መዋዕለ ነዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ቡድኑ ከኢንዱስትሪ ዞኑ አመራሮች ጋር የመከረ ሲሆን÷ ከኢንዱስትሪ ዞኑ ጋር በኢንቨስትመንቱ ዘርፍ በጋራ አብሮ ለመስራት ፍላጎት እንዳለውም ገልጿል፡፡

በተጨማሪም ልዑኩ በኢትዮጵያ ያሉትን የኢንቨስትመንት ዘርፍ ዕድል እና አማራጮችን ለዞኑ አመራሮች ገለፃ ማድረጉን ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በሌላ በኩል የኢንቨስትመንት ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ እና በቱርክ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን እና ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር አደም መሀመድ ከአዳና ግዛት ገዢ እና ከቹኮሮቫ ዩኒቨርሲቲ ዲን ጋር መክረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.