Fana: At a Speed of Life!

22ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሞሪሺየስ የሚካሄደው 22ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተጀምሯል።

ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው 28 ሴት እና 26 ወንድ በድምሩ 54 አትሌቶችን የምታሳትፍ ሲሆን÷በመክፈቻው ቀን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተለያዩ የማጣሪያ ውድድሮች ይካፈላሉ።

በ100 ሜትር ሴቶች ራሔል ተስፋዬ እና ያብስራ ጃርሶ፣ በ400 ሜትር ሴቶች ፅጌ ዱጉማ፣ አማረች ዛጎና ምስጋና ኃይሉ፣ በ400 ሜትር ወንዶች ዮብሰን ብሩ እና ዮሐንስ ተፈራ እንዲሁም በ100 ሜትር ወንዶች ሎቾ ኪዮንጋ ኢትዮጵያውያን ይሳተፋሉ።

በኮት ዶአር ናሽናል ስፖርት ኮምፕሌክስ ስታዲየም በሚካሄደው ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ከ35 በላይ የአትሌቲክስና የሜዳ ተግባራት ውድድሮች ላይ እንደምትሳተፍ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

በሞሪሺየስ በሚካሄደው 22ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከ42 አገራት የተወጣጡ 636 አትሌቶች ይሳተፋሉ ተብሏል።

ሻምፒዮናው ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኋላ ሲካሄድ የመጀመሪያው ሲሆን÷ ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2018 በናይጄሪያ አሳባ በተካሄደው 21ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና 2 የወርቅ፣ 3 የብርና 5 የነሐስ በድምሩ 10 ሜዳሊያዎች በማግኘት 4ኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቋ የሚታወስ ነው።

ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም በተካሄዱት 21ዱም የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮናዎች መሳተፏን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.