Fana: At a Speed of Life!

በግብፅ የተመዘገበው ድል የብሄራዊ ቡድኑን ጥንካሬ የሚያሳይ ነው-አሰልጣኝ ውበቱ አባተ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በግብፅ የተመዘገበው ድል የብሄራዊ ቡድኑን ጥንካሬ የሚያሳይ ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ገለጹ፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ  ቆይታውን በተመለከተ የቡድኑ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

አሰልጣኙ በመግለጫቸው ዋሊያዎቹ የግብፅን ብሄራዊ ቡድን  ከማሸነፍ በተጫማሪ ኳስ በመቆጣጠር ረገድ የተሻለ ብልጫ ማሳየት ችለዋል ብለዋል፡፡

በተለይ በግብጹ ጨዋታ ላይ የታየው የማሸነፍ ሥነ-ልቦና እና ከፍተኛ የቡድን ጥንካሬ ለተገኘው ውጤት ከፍተኛ ሚና እንደነበረው አሰልጣኙ አንስተዋል።

ብሄራዊ ቡድኑ ባደረጋቸው ሁለት ጨዋታዎች የቡድኑን መጠናከር የሚያሳዩ እንቅስቃሴዎች ታይተዋል ያሉት አሰልጣኙ÷ ብሄራዊ ቡድኑ ግብፅን ካሸነፈ በኋላ በሌሎች አገራት ቡድኖች ላይ ከፍተኛ ግምት ተሰጥቶታል ብለዋል፡፡

የማላዊው ሽንፈትን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያም ሽንፈቱ ተጫዋች በግል የፈፀሙት ስህተት መሆኑን ጠቅሰው÷ በጨዋታው ብሄራዊ ቡድኑ ከእረፍት መልስ የተሻለ መጫዎት ችሎ እንደነበር አመላክተዋል፡፡

በቀጣይ  የቻን ውድድርን ጨምሮ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ውድድሮች መኖራቸውን  እና ለዚህም ብሄራዊ ቡድኑ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በአፈወርቅ አበበ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.