Fana: At a Speed of Life!

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ኢትዮጵያ ቡና አዳማ ከተማን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ሰኔ 8፣2014 (ኤፍ ቢሲ) በ26ኛ ሳምንት የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና አዳማ ከተማን 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡

በባህርዳር ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አዳማ ከተማ እስከ እረፍት በአሜ መሀመድ ብቸናኛ ጎል ሲመራ ቢቆይም ከዕረፍት መልስ አቡበከር ናስር ያስቆጠራቸው ጎሎች ቡናማዎችን አሸናፊ አድርገዋል፡፡

ኢትዮጵያ ቡና ማሸነፉን ተከትሎ በእኩል 40 ነጥብ ከሲዳማ ቡና ጋር 3ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል፡፡

የፊት መስመር አጥቂው አቡበከር ናስር በብሄራዊ ቡድኑ ላይ ያሳየውን ማራኪ እንቅስቃሴ በ26ኛ ሳምንት የክለቡ ጨዋታ ላይም መድገም ችሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.