Fana: At a Speed of Life!

በኦስሎ የ5 ሺህ ሜትር የዳይመንድ ሊግ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በበላይነት አጠናቀዋል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦስሎ ከተማ በ5ሺህ ሜትር የተካሄደውን የዳይመንድ ሊግ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታዎች በበላይነት አጠናቀዋል፡፡
በወንዶች ምድብ በተካሄደው 5 ሺህ ሜትር የኦስሎ ዳይመንድ ሊግ ውድድር ጥላሁን ሃይሌ በአንደኝነት ሲያጠናቅቅ÷ ሳሙኤል ተፈራ እና ጌትነት ዋሌ 2ኛ እና 3ኛ ሆኖ በመግባት ውድድሩን ጨርሰዋል።
በተመሳሳይ በሴቶች ምድብ በተካሄደው የ5 ሺህ ሜትር የዳይመንድ ሊግ ውድድር ዳዊት ስዩም ርቀቱን በቀዳሚነት ስታጠናቅቅ÷ ጉዳፍ ጸጋይ እና ለተሰንበት ግደይ ደግሞ 2ኛ እና 3ኛ በመሆን ውድድሩን አጠናቀዋል፡፡
በተጨማሪም በምድቡ አትሌት ሚልኬሳ መንገሻ 5ኛ፣ አሊ አብዱልመናን 10ኛ ሆነው ማጠናቀቃቸውን ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.