Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ክልል ወጣቶች በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ5 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት ማህበራዊ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱ ይጠበቃል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በዘንድሮው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ4 ነጥብ 8 ሚሊየን በላይ ወጣቶች በመሳተፍ ከ5 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት አገልግሎት እንደሚሰጡ የክልሉ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አስታወቀ፡፡
የቢሮ ኃላፊው አቶ እርዚቅ ኢሳ እንደገለጹት÷ በክልል ደረጃ የሚካሄደው የዘንድሮ የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሐ ግብር የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት በሚገነባበት ጎርጎራ ላይ ሰኔ 28 ቀን 2014 ዓም ይጀመራል፡፡
የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሐ ግብሩም÷በዋናነት በአረንጓዴ ዐሻራና በአሸባሪው ህወሓት ወረራ ተፈጽሞባቸው በነበሩ አካባቢዎች በመልሶ ግንባታ ስራዎች ላይ ያተኩራል፡፡
ወጣቶቹ ከ800 ሚሊየን በላይ ችግኝ ከመትከል ባሻገር÷ በአሸባሪው ህወሓት የወደሙ ተቋማትን፣ የግለሰብ ቤቶችንና ሌሎች ድርጅቶችን በመገንባት የበኩላቸውን ዐሻራ እንደሚያስቀምጡም ተመላክቷል፡፡
በተጨማሪም የማጠናከሪያ ትምህርት መስጠት፣ የማህበረሰብ ጤና ማካሄድ፣ የአቅመ ደካሞችን ቤት መጠገን፣ የወሳኝ ኩነት መረጃን ማጠናቀር በወጣቶቹ የሚከናወኑ ተግባራት መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወጣቱ በህልውና ዘመቻው ያሳየውን ተነሳሽነት በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሐ ግብር ላይ በንቃት እንዲደግመውም አቶ እርዚቅ ኢሳ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የዘንድሮው የክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ከ24 የመንግስት ተቋማትና የልማት ድርጅቶች ጋር በመተባበር የሚከናወን መሆኑም ተገልጿል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.