Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ የ25 አቅመ ደካማ ወገኖች የመኖሪያ ቤት እድሳት ሥራ ተጀመረ

አዲ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ የመንግሥት ተቋማት በመዲናዋ በከፋ ችግር ውስጥ የሚገኙ የ25 አቅመ ደካማ ወግኖችን የመኖሪያ ቤቶች እድሳት አስጀመሩ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት ኮሚሽን 15 እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማት እና ቤቶች ኮርፖሬሽን ቢሮዎች ደግሞ 10 የአቅመ ደካማ ቤቶችን እድሳት ዛሬ አስጀምረዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ዳዲ ወዳጆ እንደገለጹት÷ ቤቶቹ ባለሀብቶችንና የልማት አጋሮችን በማስተባበር የሚሰሩ ናቸው፡፡
ነዋሪዎችን፣ ባለሀብቶችንና ሌሎች የልማት አቅሞችን በማስተባበር የአቅመደካሞችን ችግር መፍታት እንደሚቻል ጠቁመው÷ ፕላንና ልማት ኮሚሽንም ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት በክረምት በጎ ፈቃድ 15 የአቅመ ደካማ ቤቶችን እድሳት አስጀምሯል ማለታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡
በተመሳሳይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማት እና ቤቶች ኮርፖሬሽን ቢሮዎች÷ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ቢሮና ቤቶች ኮርፖሬሽን በስራቸው የሚገኙ የስራ ተቋራጮችን በማስተባበር በ3 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ወጪ የሚያስገነቡት 10 መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ተጀምሯል፡፡
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሪት ያስሚን ወሃብረቢ በመርሐ ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ተባብረንና ተጋግዘን በመስራት ችግሮቻችንን እናቃልላለን ብለዋል፡፡
የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ሽታዬ መሀመድ÷ በከፋ ሁኔታ ውስጥ ኑሯቸውን የሚገፉ ወገኖችን መኖሪያ ቤት በአዲስ መልክ ለመገንባት የተረከቡ አካላት አርያነት ያለው ተግባር መፈጸማቸውን ጠቁመው÷ ዛሬ የተጀመሩ ቤቶችን በአጠረ ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እንዲረግ መጠየቃቸውን የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ መረጃ ያመላክታል፡፡
ስራውን የተረከቡትን ተቋራጮች ወክለው ንግግር ያደረጉት ኢንጂነር እስክንድር አክሊሉ ÷ የወገኖቻችን ችግር የራሳችን ችግር አድርገን በመውሰድ በልዩ ትኩረት እንሠራለን ብለዋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.