Fana: At a Speed of Life!

ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ የትምህርትመስኮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች እያስመረቁ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች በዛሬው ዕለት አስመርቀዋል፡፡
የአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ በመጀመሪያ ዲግሪ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪ በመደበኛ፣ በተከታታይ የማታና በእረፍት ቀናት ያስተማራቸውን ከ1 ሺህ 400 በላይ ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡
ጅማ ዩኒቨርሲቲም በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች በመጀመሪያ፣ በሁለተኛ እና በዶክተሬት ዲግሪ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመርቋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው በአጠቃላይ 2 ሺህ 509 ተማሪዎችን ያስመረቀ ሲሆን፥ ከእነዚህ ውስጥም ስምንቱ በዶክተሬት ድግሪ የተመረቁ የውጭ ዜጎች መሆናቸው ተመላክቷል፡፡
በተመሳሳይ የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ለ67 ኛ ጊዜ በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያ ዲግሪ፣ በሁለተኛ እና በዶክትሬት ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 1ሺህ 800 በላይ ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡
ዲላ ዩኒቨርሲቲ እና ወልቂጤ ዩኒቨርስቲም በመደበኛው፣ በክረምት እና በዕረፍት ቀናት መርሐ ግብሮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች አስመርቀዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው በመጀመሪያ፣ በሁለተኛ እና በሶስተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 650 ተማሪዎችን ነው ያስመረቀው ።
የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ እና የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲዎችም በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች አስመርቀዋል፡፡
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለ38ኛ ጊዜ በህክምና ዘርፍ ያሰለጠናቸውን 281 እጩ ዶክተሮችን በዛሬው ዕለት አስመርቋል፡፡
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲም ለ35ኛ ጊዜ በተለያዩ የሙያ መስክ ያሰለጠናቸውን ከ2 ሺህ 500 በላይ ተማሪዎችን ነው ያስመረቀው፡፡
በተመሳሳይ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ የትምህርት መርሐ ግብር በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 997 ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በበኩሉ ለ23 ኛ ዙር በተለያዩ የትምህርት መስኮችያሰለጠናቸውን ከ6 ሺ 471 በላይ ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡
በስነ ስርዓቱ 4 ሺህ 795 በመጀመሪያ ዲግሪ፣ 1ሺህ 604 በሁለተኛ ዲግሪ፣ 18 በሶስተኛ ዲግሪ እንዲሁም ልዩ የመምህራን ስልጠና የወሰዱ ተማሪዎች መመረቃቸው ተገልጿል፡፡
አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጅ ዩኒቨርስቲም በተለያዩ መስኮች ሲያሰለጥናቸው የቆዩ 1ሺህ 253 ተማሪዎችን
አስመረቋል፡፡
በሌላ በኩል በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የፀጥታ ችግር ምክንያት ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ ሀዋሳ ዮኒቨርሲቲው ተዘዋውረው ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ከነበሩ 1 ሺህ 320 ተማሪዎች ውስጥ 447 ተማሪዎችም በዛሬው ዕለት ተመርቀዋል፡፡
በአብዱረህማን መሃመድ፣ በቢቂላ ቱፋ፣ በሰላም አስመላሽ፣ በተሾመ ኃይሉ፣ በእዮናዳብ አንዱዓለም፣ በጌትነት ጃርሳ፣ በብርሃኑ በጋሻው፣   በተመስገን ቡልቡሎ እና በፌቨን ቢሻው
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.