አስተዳደሩ የ14ኛ ዙር የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ አወጣጥ ስነ-ስርዓትን ለአርብ መዛወሩን አስታወቀ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 29 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ14ኛው ዙር የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ አወጣጥ ስነስርዓት ለአርብ መዛወሩን አስታወቀ።
ከተማ አስተዳደሩ ዕጣ አወጣጥ ስነስርአቱን በነገው እለት ለማካሄድ ፕሮግራም ይዞ እንደነበር ይታወቃል፡፡
ነገር ግን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጠራው ስብሰባ ምክንያት የዕጣ አወጣጥ ስነስርዓቱ ወደ ፊታችን አርብ ሃምሌ 1 ቀን 2014 ዓ.ም የተዛወረ መሆኑን ከይቅርታ ጋር አስታውቋል።
አስተዳደሩ ታዛቢዎች፣ ባለእድለኞች እና ሌሎችም በክብር እንግድነት ለሚገኙ እንግዶች እና የሚዲያ አካላት ለተፈጠረው የፕሮግራም ለውጥ ይቅርታ ጠይቋል።
በዚህም ሁሉም አካላት በተለዋጩ ፕሮግራም መሰረት እንዲገኙ ጥሪ ማቅረቡን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ፅህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።