Fana: At a Speed of Life!

የ2014 ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የማጠቃለያ እና የኮከቦች ሽልማት መርሐ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2014 ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የማጠቃለያ እና የኮከቦች ሽልማት መርሐ ግብር ተካሄደ፡፡
በመርሐ ግብሩ የባህል እና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጀላ መርዳሳ፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳይያስ ጂራ፣ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር የቦርድ ሰብሳቢ መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
በተካሄደው የሽልማት መርሐ ግብር ላይ የውድድር ዓመቱ ምርጥ ተጫዋች በመሆን÷ ጋቶች ፓኖም የ210 ሺህ ብር እና የማስታወሻ ዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል፡፡

እንዲሁም የዓመቱ ውድድር ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ በመሆን ደግሞ ይገዙ ቦጋለ የዋንጫ እና የ200 ሺህ ብር ተሸላሚ ሆኗል።

የ2014 የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ምርጥ ግብ ጠባቂ በመሆን÷ የቅዱስ ጊዮርጊሱ ቻርለስ ሉክዋጎ ተመርጧል።
ዩጋንዳዊው ግብ ጠባቂ በተወካዩ አማካይነት 150 ሺህ ብር እና የዋንጫ ሽልማት ከቀድሞው ግብ ጠባቂ በለጠ ወዳጆ እጅ ተረክቧል።
የዓመቱ ምርጥ ዋና ዳኛ በመሆን ዶክተር ኃይለየሱስ ባዘዘው የ105 ሺህ ብር እና የዋንጫ ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡
የዓመቱ ምርጥ ረዳት ዳኛ በመሆን ደግሞ ትግል ግዛው የ105 ሺህ ብር እና የዋንጫ ሽልማቱን ከቀድሞ ዳኛ ይግዛው ብዙአየሁ እጅ ተቀብሏል።
በሌላ በኩል የሊጉ አክሲዮን ማኅበር ለተሳታፊ ክለቦች እንደየ ደረጃቸው መጠን ገንዘብ ማከፋፈሉንም ሶከር ኢትዮጵያ ገልጿል፡፡
የውድድር ዓመቱ ምርጥ ወጣት ተጫዋች ሆኖ የተመረጠው ዓመቱን በሀዋሳ ከተማ ጀምሮ በጅማ አባጅፋር ያገባደደው አላዛር ማርቆስ 105 ሺህ ብር እና ዋንጫ ተሸልሟል፡፡

በአሰልጣኝነት ዘርፍ÷ የ2014 ቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ምርጥ አሠልጣኝ በመሆን የቅዱስ ጊዮርጊስ አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ የ200 ሺህ ብር እና የክብር ዋንጫውን ተሸልሟል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.