Fana: At a Speed of Life!

ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በተለያየ ሙያ ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎቻቸውን አስመረቁ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በተለያየ ሙያ ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎቻቸውን አስመርቀዋል፡፡

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ እና በበማታው የትምህርት መርሐ ግብር ያስተማራቸውን 974 ተማሪዎች አስመርቋል፡፡

ዩኒቨርስቲው በአሁኑ ወቅት ከ14 ሺህ 679 ተማሪዎችን በማስተማር ላይ ይገኛል፡፡

በተመሳሳይ÷የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በተለያየ የሙያ ዘርፍ ያሰለጠናቸውን 4 ሺህ 400 በመጀመሪያ እና በድህረ ምረቃ መርሐ ግብር ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመርቋል፡፡

በሌላ በኩል÷ የአማራ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት በ2014 ዓ.ም በአራት የትምህርት ዘርፎች ለሁለተኛ ዙር በሁለተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን የሥራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎችን ርዕሰ መስተዳድር  ዶክተር ይልቃል ከፋለ በተገኙበት ማስመረቁን አሚኮ ዘግቧል፡፡

በተመሳሳይ ወለጋ ዩንቨርሲቲ በተለያየ ሙያ ያሰለጠናቸውን÷ በመጀመርያ ዲግሪ 1 ሺህ 146፣ በሁለተኛ ዲግሪ 302 እንዲሁመ በሦስተኛ ዲግሪ ደግሞ ስምንት በአጠቃላይ 1 ሺህ 458  ተማሪዎች አስመርቋል፡፡

በሙሉጌታ ደሴ እና ገላና ተስፋ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.