Fana: At a Speed of Life!

አፈጉባኤ አገኘሁ ተሻገር ከደቡብ ኮሪያ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ11፤ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር የኢትዮጵያ እና የደቡብ ኮሪያን የቆዬ ወዳጅነት ለማጠናከር በኢትዮጵያ የደቡብ ኮሪያ አምባሳደር ካንግን ጋር ተወያዩ፡፡

ኢትዮጵያና ኮሪያ የረጅም ጊዜ ታሪካዊ ግንኙነት እንዳላቸው በውይይቱ ወቅት ተገልጿል፡፡

ኢትዮጵያ ከ6 ሺህ በላይ የሚሆን መከላከያ ሠራዊት በመላክ ለኮሪያ ሰላም ትልቅ አስተዋፅኦ ማበርከቷን የጠቀሱት አቶ አገኘሁ ተሻገር÷ አሁናዊው የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት መልካምና የሚበረታታ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ግንኙነቱ በልማት፣ በትምህርትና ስልጠና፣ በንግድ እንዲሁም በኢንቨስትመንት ዘርፎች የሚገለፅ ነው ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ የገጠማትን ጦርነት በሠላማዊ መንገድ መፈታት አለበት የሚል ፅኑ እምነት እንዳላት አፈጉባዔው ስለ ኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ በገለጹበት ወቅት ጠቁመዋል፡፡

አምባሳደር ካንግ በበኩላቸው ሁለቱ ሀገራት በተለያዩ ዘርፎች መልካም ትብብርና ግንኙነት እንዳላቸው ጠቅሰው÷ መንግስታዊ የትብብር ፕሮጀክቶችን እንደምሳሌ አንስተዋል፡፡

በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድ፣ ኢንቨስትመንትና በሌሎች ዘርፎች ያሉትን መልካም ግንኙነቶች ሀገራቸው ይበልጥ አጠናክራ መቀጠል እንደምትፈልግ ገልጸዋል፡፡

ደቡብ ኮሪያ በሰሜን ኢትዮጵያ ተከስቶ የነበረው ጦርነት በሠላማዊ መንገድ መፈታት አለበት ብላ እንደምታምን ጠቁመው÷ ለተጀመረው የሠላም እንቅስቃሴም ተገቢውን ድጋፍ ታደርጋለች ማለታቸውን ከፌዴሬሽን ምክር ቤት የተገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.