Fana: At a Speed of Life!

ንጋት ላይ በተካሄዱ ውድድሮች ኢትዮጵያ ሁለት የብር ሚዳሊያዎች አገኘች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ18ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሴቶች በ1 ሺህ 500 ሜትር ፍፃሜ በጉዳፍ ፀጋይ ኢትዮጵያ ሶስተኛውን የብር ሜዳልያ አገኘች።

በውድድሩ ኬንያ የወርቅ እና ብሪታኒያ የነሃስ ሜዳሊያ አገኝተዋል።

በወንዶች 3 ሺህ ሜትር መሰናክል ለሜቻ ግርማ ሁለተኛ በመውጣት ለኢትዮጵያ የብር ሜዳሊያ አስገኝቷል።

አትሌት ለሜቻ ግርማ ርቀቱን በሁለተኛነት ለመጨረስ 8፡26.01 ወስዶበታል።

በውድድሩ የሞሮኮ አትሌት የወርቅ እና የኬንያ አትሌት የነሃስ ሜዳሊያ አግኝተዋል።

በሻምፒዮናው ኢትዮጵያ እስካሁን ሶስት የወርቅ እና ሶስት የብር ሜዳሊያዎችን አግኝታለች።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.