Fana: At a Speed of Life!

11ኛው የአፍሪካ በይነመረብ አስተዳደር ጉባዔ በማላዊ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 11ኛው የአፍሪካ በይነመረብ አስተዳደር ጉባዔ በማላዊ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
በጉባዔው ከሁሉም የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ ባለድርሻ አካላት የበይነመረብ አስተዳደርን አስመልክቶ የሚመክሩበት እንደሆነ ተገልጿል።
“በይነ-መረብ ለሰው ልጆች ጥንካሬና አብሮነት!” በሚል መሪቃል እተካሄደ ባለው በዚህ ጉባዔ ተመጣጣኝና ትርጉም ያለው የበይነ መረብ ተደራሽነትን፣ የመረጃ መረብ ደህንነትን፣ የግል ዳታ ጥበቃን፣ የዲጂታል ክህሎትን እና መሰረተ ልማትን በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ነው ውይይቱ እየተደረገ ያለው፡፡
በመድረኩ እየተሳተፉ የሚገኙት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ÷ ኢትዮጵያ በቀጣይ ዓመት ለምታስተናግደው 17ኛው ዓለምአቀፍ የኢንተርኔት አስተዳደር ጉባዔ ዝግጅት ተሞክሮዎችን የምታገኝበት መድረክ እንደሆነ ገልጸዋል።
ሚኒስትር ዴኤታዋ በበይነ መረብ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ላይ በሚደረጉ ውይይቶችና ውሳኔዎች ላይ አፍሪካ እንደ አህጉር ንቁ ተሳታፊ መሆን ይገባታል ብለዋል።
ኢትዮጵያ በቀጣይ ዓመት በምታስተናግደው ዓለምአቀፍ የበይነ-መረብ አስተዳደር ጉባዔ ላይ እንዲሳተፉም ለጉባዔው ታዳሚዎች ግብዣ አቅርበዋል።
17ኛው ዓለም አቀፍ የበይነመረብ አስተዳደር ጉባዔ ከህዳር 19 እስከ ሕዳር 23/2015 ዓም ድረስ በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.