አትሌቶቻችን በድላቸው ኢትዮጵያውያን አንገታችንን በያለንበት ቀና እንድናደርግ አድርገውናል- ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአትሌቶቻችን ድል ኢትዮጵያውያን በያለንበት አንገታችንን ቀና እንድናደርግ ያደረገ መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ተናገሩ፡፡
ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ በአትሌቶች አቀባበል እና የምስጋና መርሐ ግብር ላይ ተገኝተው የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በመልዕክታቸውም፥ አትሌቶቻችን በሐምሌ ክረምት ጭጋግ ውስጥ በሀገራችን ደማቅ ብርሃን እንዲያበራ አድርገውልናል ፤ የሀገራችንን ስም በበጎ አስነስተውልናል ብለዋል፡፡
ሆኖም ድሉ ከሜዳሊያ ያለፈ ነው ያሉት ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ፥ ድሉ ለተጨነቀው ላዘነው ለተከዘው፣ ኑሮ ለከበደው፣ እንደሀገር የት ነን ለሚለው ፈገግታን ያስገኘ ነው ብለዋል፡፡
ለመከፋፈል ቢሞከርም በህዝብ ደረጃ ችግር እንደሌለ አሳይታችኋል ያሉት ፕሬዚዳንቷ፥ ድሉ በድቅድቅ ጨለማ ብርሃን እንዳለ አመልካች ነው ብለዋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!