Fana: At a Speed of Life!

የተገኙት ጀግና አትሌቶች የቀድሞ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የትውልድ ቅብብሎሽ ውጤት ናቸው – ኮሎኔል ደራርቱ ቱሉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቀጣይ በሚደረጉ ውድድሮች የኢትዮጵያ አትሌቶችን የሜዳሊያ ብዛት ከፍ ለማደረግ እንደሚሰራ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮሎኔል ደራርቱ ቱሉ ተናገረች፡፡

በአሜሪካ ኦሪገን በተካሄደው 18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተመዘገበውን አኩሪ ድል በማስመልከት የአትሌቶች የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል መርሐ ግብር በብሄራዊ ቤተ መንግስት እየተካሄደ ነው፡፡

በመርሐ ግብሩ ንግግር ያደረገችው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮሎኔል ደራርቱ ቱሉ ፥ ጀግኖች ኢትዮጵያውን አትሌቶች በተለያዩ ጫናዎች ውስጥ ሆነው ከፍተኛ ድል ማስመዝገባቸውን ገልፃለች፡፡

ኢትዮጵያ በዓለም አደባባይ ስሟ ከፍ እንዲል ያደረጉ አሁን ላይ የተገኙ ጀግና አትሌቶች የቀድሞ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የትውልድ ቅብብሎሽ ውጤት ናቸው ብላለች፡፡

የአትሌቲክስ ልዑካን ቡድን በኦሪገን ቆይታው የተሳካ ጊዜን እንዲያሳልፍ አስተዋፅዖ ላደረጉ ተቋማትና ግለሰቦች ፕሬዚዳንቷ ምስጋናዋን አቅርባለች፡፡

በኦሪገን ኢትዮጵያ አሸንፋለች ያለቸው ደራርቱ በቀጣይ በሚደረጉ ዓለማቀፋዊ ውድድሮችም የኢትዮጵያውያን አትሌቶችን የሜዳሊያ ብዛት ከፍ ለማድረግ ይስራል ብላለች፡፡

በሚኪያስ አየለ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.