Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ነቢል በጋራና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ከደቡብ ሱዳን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ሪክ ማቻር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል ማህዲ በጋራና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ከደቡብ ሱዳን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ሪክ ማቻር ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይቱ አምባሳደር ነቢል በኢትዮጵያ ስላለው ለውጥ ያብራሩ ሲሆን ፥ መንግስት ለውይይት እና ለሰላም ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር እያደረገ ያለውን ጥረት እንዲሁም የሰብዓዊ እርዳታ አሰጣጥን አስመልክቶ ለተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንቱ ገለጻ አድርገዋል።

አክለውም የሰላም ስምምነቱ የተከናወኑ ተግባራትን በተሟላ መልኩ ለማስፈጸም ጠቃሚ መሳሪያ ነው ተብሎ እምነት የተጣለበትን ረቂቅ ፍኖተ ካርታ አድንቀዋል።

ስምምነቱ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንዲሆን ኢትዮጵያ ያላትን ቁርጠኝነት መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንቱ በኢትዮጵያ እየታየ ያለውን አወንታዊ ለውጥ አድንቀው ፥ በደቡብ ሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ለአምባሳደሩ ገለጻ አድርገዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.