Fana: At a Speed of Life!

የተለያዩ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር አከናወኑ

 

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጀላ መርዳሳ እና የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር አከናውነዋል፡፡

የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበልና የፌዴራል ከፍተኛ አመራሮች በሀዋሳ ኢንደስትሪያል ፓርክ ነው የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ያካሄዱት፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ የሲዳማ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በመገኘት የፓርኩን የስራ እንቅስቃሴ ተመልክተዋል።

አቶ መላኩ አለበል እና የሲዳማ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በፓርኩ በተለያዩ መስኮች ከተሰማሩ ባለሀብቶች ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በሌላ በኩል የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማቱ በይርጋለም ከተማ የአረንጓዴ ዐሻራና የአቅመ ደካሞች ቤት የማደስ ተግባራትን ያከናወኑ ሲሆን÷ በመርሐ ግብሩ ላይም የባህልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጀላ መርዳሳን ጨምሮ የሲዳማ  ክልል ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጀጎ አገኘሁና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል።

እንዲሁም የሐረሪ ክልል ምክር ቤት አባላት የተጠናቀቀው የክልሉ ምክር ቤት ጉባኤ የማጠናቀቂያ መርሐ ግብር አካል የሆነውን የችግር ተከላ መርሐ ግብር አከናውነዋል፡፡

የክልሉ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ጌቱ ነገዎ እንደገለፁት÷ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩ በዋናነት የምክር ቤቱ አባላት ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በጋራ በመሆን አሻራቸውን ለማሳረፍ አልሞ የተዘጋጀ ነው።

በመርሐ ግብሩም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ወይዘሮ ሚስራ አብደላ የክልሉ ዋና አፈ-ጉባኤ አቶ ሱልጣን አብዱሰላም ጨምሮ ሌሎች የምክር ቤቱ አባላትና ከፍተኛ አመራሮች መገኘታቸውን ከሐረሪ ክልል ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.