Fana: At a Speed of Life!

1ሺህ 76 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1ሺህ 76 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡
ዛሬ በሦስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳዑዲ ዓረቢያ የመመለስ ሥራ 1ሺህ 76 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ የተቻለ ሲሆን÷ ከእነዚህ ውስጥ አምስቱ ታዳጊዎች መሆናቸው ተገልጿል፡፡
ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢው ድጋፍ እና እንክብካቤ ተደርጎላቸው ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማዕከላት መሄዳቸውን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
እስካሁን ድረስ በተከናወነ ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ሥራ 61 ሺህ 449 ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉ ተመላክቷል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.