Fana: At a Speed of Life!

በከተሞች የመሠረተ ልማት እቅዶችን ውጤታማ ለማድረግ ሰፊ ጥረት ተደርጓል -አቶ ተስፋዬ ይገዙ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በከተሞች የተጓተቱ ፕሮጀክቶችን በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ ለማጠናቀቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎች ማከናወን ተችሏል ሲሉ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ይገዙ ተናገሩ፡፡
 
በደቡብ ክልል የከተሞች ተቋማዊና መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም ጉባኤ በአርባምንጭ ከተማ እየተካሔደ ነው፡፡
 
በደቡብ ክልል በዓለም ባንክ ድጋፍ ትግበራ የከተሞች ተቋማዊና የመሠረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም /ዩአይአይዲፒ/ በክልሉ በተመረጡ 17 ከተሞች የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች ተግባራዊ በመደረግ ላይ ናቸው።
 
ወቅታዊ እና ጥራት ያለው የግዢ ስርዓት ተከትለው አሰራራቸውን ለማዘመን ጥረት ያደረጉ ከተሞችን መፍጠር መቻሉንም የቢሮ ኃላፊው አብራርተዋል።
 
በክልሉ ባለፈው ዓመት ዘጠኝ ከተሞች ነቀፌታ የሌለው ኦዲት መደረጋቸውንም ነው የተናገሩት።
 
የመሠረተ ልማት እቅዶችን ውጤታማ ለማድረግ ጥረት መደረጉን የተናገሩት አቶ ተስፋዬ፥ የተጓተቱ ፕሮጀክቶችን በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ ለማጠናቀቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎች ማከናወን እንደተቻለም አብራርተዋል።
 
በበጀት ዓመቱ ከ256 የልማት ፕሮጀክቶች ውስጥ 212 የኮንትራት ሥራዎች የተጠናቀቁ ሲሆን፥ ቀሪ 41 ኮንትራቶች ወደ 2015 በጀት ሓመት መዛወራቸውን ከክልሉ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ዘገባ ለማወቅ ተችሏል።
 
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.