Fana: At a Speed of Life!

በምዕራብ አርሲ ዞን “አርዳይታ” ምርጥ ዘር እርሻ ልማት አካባቢ ለሚኖሩ የሕብረተሰብ ክፍሎች የ 5 ሚሊየን ብር ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን በ”አርዳይታ” ምርጥ ዘር እርሻ ልማት አካባቢ ለሚኖሩ የሕብረተሰብ ክፍሎች  የ5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡

ድጋፉም በምዕራብ አርሲ ዞን ‘አርዳይታ’ ምርጥ ዘር እርሻ ልማት አጎራባች ለሚገኘው የ’ወልተኢ’ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማስፋፊያ እና ለ’ወልተኢ’ ቀበሌ ኤሌክትሪክ ሀይል ማስገቢያ የሚውል ነው ተብሏል።

ድጋፉን የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ክፍሌ ወልደማርያም እና ሌሎች የስራ ሃላፊዎች ለአከባቢው የአገር ሽማግሌዎችና ተወካዮች አስረክበዋል።

የአከባቢው ነዋሪዎችም ለተደረገላቸው ድጋፍ አመስግነው÷  ኮርፖሬሽኑ የጀመረውን ስራ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

በሌላ በኩል የኮርፖሬሽኑ አመራሮችና ሰራተኞች በአርዳይታ ምርጥ ዘር እርሻ ልማት ግቢ ውስጥ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ማከናወናቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.