Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ስለሺ በቀለ ከአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 11 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስለሺ በቀለ ከአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ማይክል ሐመር ጋር ተወያዩ።

በዚህ ወቅትም በኢትዮጵያ ከዘላቂ ሰላም ግንባታ፣ ሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦት፣ ተጠያቂነትንና ዴሞክራሲን ከማስፈን፣ ብሄራዊ ውይይት እና ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ሃሳብ ተለዋውጠዋል።

በውይይታቸው ወቅት በተነሱ ጉዳዮች ዙሪያ ባሉ መሻሻሎች እና ባጋጠሙ ተግዳሮቶች ዙሪያ ሃሳብ መለዋወጣቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

አምባሰደር ስለሺ በውይይታቸው ልዩ መልዕክተኛው ከኢትዮጵያ የስራ ሃላፊዎች ጋር ላላቸው ግንኙነት እና የቆየውን የሀገራቱን ግንኙነት ለማጠናከር ላደረጉት ጥረት አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

ልዩ መልዕክተኛው በበኩላቸው በኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ ባዩት አበረታች ለውጥ መደሰታቸውን ለአምባሳደር ስለሺ ገልጸውላቸዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.