Fana: At a Speed of Life!

ሊዲያ ታፈሰ ለዓለም ከ17 ዓመት በታች ዋንጫ ውድድር ጥሪ ቀረበላት

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዳኛ ሊዲያ ታፈሰ በህንድ አስተናጋጅነት በሚካሄደው የዓለም ሴቶች ከ17 ዓመት በታች ዋንጫ ውድድር ላይ አገልግሎት እንድትሰጥ በፊፋ ጥሪ ቀረበላት፡፡

የዓለም ከ17 ዓመት በታች የሴቶች ዋንጫ ጨዋታ ውድድር ከጥቅምት 1 እስከ ጥቅምት 20 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ በህንድ አስተናጋጅነት ይካሄዳል፡፡

የውድድሩ የበላይ አካል የሆነው ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል (ፊፋ) በዳኝነት የሚያገለግሉ ዳኞችን ከተለያዩ ሀገራት መምረጡንም ይፋ አድርጓል፡፡

14 ዋና፣ 28 ረዳት እና 16 የቪዲዮ ዳኞችን ዝርዝር ይፋ ሲያደርግ ከአፍሪካ ሁለት የቪዲዮ ዳኞች ተካተዋል፡፡

በዚሁ መሰረት ኢትዮጵያዊቷ ዳኛ ሊዲያ ታፈሰም ከአፍሪካ ከተመረጡ ሁለት የቪዲዮ ዳኞች መካከል አንዷ ሆናለች፡፡

ሌላኛዋ የኢሲዋቲኒ ዜግነት ያላት ቪያና ሊቺያ የቪዲዮ ዳኝነት አገልግሎት የምትሰጥ ይሆናል ሲል ሶከር ኢትዮጵያ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.