Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ባጫ ደበሌ ከኢትዮ- ኬንያ የወዳጆች ማህበር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮ-ኬንያ ወዳጆች ማህበር በኬንያ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ጄኔራል ባጫ ደበሌ ጋር በቀጠናው ሰላምና ልማት ዙሪያ ውይይት አድርጓል፡፡

የኢትዮ-ኬንያ ወዳጆች ማህበር በኬንያ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር በመተባበር በቀጣናው ሰላምና ልማት ላይ በቅርበት እንደሚሰራም ገልጿል፡፡

አምባሳደር ባጫ ደበሌ ከማህበሩ ሊቀመንበር ኤች ደብሊው ጆ አሌች ጋር ባደረጉት ውይይት፥ ኤምባሲው በኢትዮጵያና ኬንያ መካከል የሚካሄዱ የሰላምና የልማት ፕሮጀክቶችን በመደገፍ ከማህበሩ ጋር በቅርበትና በትብብር ለመስራት ዝፍግጁ መሆኑን አረጋግጠውላቸዋል።

በሁለቱ እህትማማች ሀገሮች መካከል ያለውን ጠንካራ የሕዝብ- ለሕዝብ ግንኙነትም ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ ሊቀመንበሩ እያደረጉ ላሉት ጥረት በኢትዮጵያ መንግሥት ስም አመስግነዋል።

አምባሳደሩ ለማህበሩ አባላት ባደረጉት ገለጻ ፥ የኢትዮጵያ መንግሥት በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር ለሚደረገው የሰላም ጥረት “ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄዎች” የሚለው የፓን አፍሪካ መርህ በመጥቀስ ለሰላም ቁርጠኛ መሆኑን አስረድተዋል።

አያይዘውም ፥ ህወሓት ለሰላም የቆመ ኃይል እንዳልሆነና የትግራይን ወጣቶች በግዳጅ በመመልመል የፓለቲካ ዓላማውን እያራመደ እንደሚገኝ አብራርተዋል።

የማህበሩ ሊቀመንበር በበኩላቸው ፥ በቀጣናው ሰላምና ልማትን ለማስፈን እጅ ለእጅ ተያይዞ መስራት እንደሚያስፈልግ በአጽንኦት መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ሊቀመንበሩ አክለውም ‘ሰላምና ብዝሃነት በጋራ ልናሸንፍባቸው የሚገቡ የህብረተሰብ ዋነኛ ገጽታዎች ናቸው ብለዋል።

የኢትዮ-ኬንያ ወዳጆች ማህበር በኢትዮጵያና በኬንያ መካከል ሰላምን፣ ወዳጅነትን እና ልማትን ለማስፈን በፈረንጆቹ 2020 የተመሰረተ ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.