Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ህወሓት ለተቸገሩ የትግራይ ክልል ወገኖች ወደ ክልሉ የሚላክን ምግብ ለጦርነት እየተጠቀመ መሆኑ ተረጋገጠ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት ለምግብ እህል እጥረት ለተጋለጡ የትግራይ ክልል ወገኖች ወደ ክልሉ የሚገባን የምግብና ሌሎች ቁሳቁሶች ለጦርነት እየተጠቀመ መሆኑ ተረጋገጠ።
የሽብር ቡድኑ ሰሞኑን የከፈተውን ሶስተኛ ዙር ጦርነት ተከትሎ ሸሽቶ በሄደባቸው አካባቢዎች እና ምሽጎች ላይ ዓለም አቀፍ የረድኤት ድርጅቶች ለተቸገሩ የትግራይ ወገኖች የለገሷቸውም ዱቄት፣ አልሚ ምግቦች እና ሌሎች ቁሳቁሶች በመገኘት ላይ ናቸው።
የህወሓት የሽብር ቡድን የእርዳታ እህልንና ቁሳቁስን በመዝረፍ ለጦርነት ተግባሩ ሲያውል ይህ የመጀመሪያው አለመሆኑ ነው የሚታወቀው።
ከዚህ ቀደም የሽብር ቡድኑ በአማራ እና አፋር ክልሎች በፈፀማቸው ወረራዎች፥ ታጣቂዎቹ ችግር ላይ ከወደቁ የክልሉ ነዋሪዎች ጉሮሮ የተቀሙ አልሚ ምግቦችን ሲጠቀሙ እንደነበር በመረጃ ተረጋግጧል።
የአሁኑን ጦርነት ሲከፍትም መቀሌ ከሚገኘው የዓለም ምግብ ፕሮግራም መጋዘን እርዳታን ለማሰራጨት ይውል የነበረን 570 ሺህ ሊትር ነዳጅ መዝረፉ አይዘነጋም።
ይህም የእርዳታ ቁሳቁስን ለጦርነት ለማዋል የፈፀመው ዝርፊያ በተመድ እና በሀገራት ውግዘትን እንዳስከተለበት ይታወቃል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.