Fana: At a Speed of Life!

በትምህርት ዘርፉ አዲስ የትምህርት ፖሊሲ በማዘጋጀት የተግባር እንቅስቃሴ መጀመሩ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በትምህርት ዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ አዲስ የትምህርት ፖሊሲ በማዘጋጀት የተግባር እንቅስቃሴ መጀመሩን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ ተናገሩ።

ሚኒስትሩ ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ማሀበረሰብ ጋር ምክክር አድርገዋል።

በዚህ ወቅትም በኢትዮጵያ እየተስተዋሉ ላሉ ችግሮች ከዚህ ቀደም የነበረው የትምህርት ፖሊሲ ምክንያት መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

የትምህርት ስርዓቱ በብዙ ችግሮች የተበተበ መሆኑን የጠቆሙት ሚኒስትሩ፣ በመማር ማስተማሩ የሚስተዋሉ የትምህርት ጥራት ችግሮች ብቃትና እውቀት ያለው ትውልድ ማፍራት እንዳይቻል ማድረጉንም አንስተዋል።

በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ 47 ሺህ ትምህርት ቤቶች ውስጥ 0 ነጥብ 01 በመቶ ወይም ስድስቱ ብቻ እነሱም በአዲስ አበባ የሚገኙ አስፈላጊውን መስፈርት አሟልተው እያስተማሩ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ይህን ችግር ለመቅረፍም አዲስ የትምህርት ፖሊሲ በማዘጋጀት በትምህርት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ የተግባር እንቅስቃሴ ውስጥ መገባቱን አመላክተዋል።

በመቅደስ ደረጀ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.