በናይል ወንዝ ውሃ ፍትሐዊ አጠቃቀም ላይ ያተኮረ ጉባኤ እየተካሄደ ነው
አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በናይል ወንዝ ውሃ ፍትሐዊ አጠቃቀም ላይ ያተኮረ የተፋሰሱ ሀገራት ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
በጉባኤው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ የተፋሰሱ ሀገራትና የቀጣናው የዘርፉ ተቋማት ተወካዮች፣ በተፋሰሱ ሀገራት የሚገኙ ከሰባት በላይ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶችና የናይል ጉዳይ ተመራማሪዎች ተገኝተዋል።
ለሦስት ቀናት በሚቆየው በዚሁ ጉባኤ በናይል ውሃ ፍትሐዊ አጠቃቀም ላይ ያተኮሩ ጥናቶች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!