Fana: At a Speed of Life!

ለጥምር ጦሩ እየተደረገ ያለው ድጋፍ ለሠራዊቱ አቅም እና ብርታት ፈጥሯል- ሜ/ ጄነራል ጥሩዬ አሰፌ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በወሎ ግንባር ለሚገኘው ጥምር ጦር እየተደረገ ያለው ድጋፍ ለሠራዊቱ ታላቅ አቅም እና ብርታት እንደፈጠረለት የወሎ ግንባር ሎጂስቲክስ ኃላፊ ሜጀር ጄነራል ጥሩዬ አሰፌ ተናገሩ።

የደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር በግንባር እየተፋለመ ለሚገኘው ጥምር ጦር የአዲስ ዓመት በዓልን ምክንያት በማድረግ 22 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የአይነት ድጋፍ አድርጓል፡፡

ድጋፉ በዞኑ አስተዳደር ስር ከሚገኙ 20 ወረዳወች እና ዘጠኝ ከተማ አስተዳደሮች የተሰበሰበ ሲሆን፥ የደቡብ ወሎ ዞን የሰበሰበውን ድጋፍ ዛሬ በወልድያ ከተማ ተገኝቶ አስረክቧል፡፡

የወሎ ግንባር ሎጂስቲክስ ኃላፊ ሜጀር ጄነራል ጥሩዬ አሰፌ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ በወሎ ግንባር ለሚገኘው ጥምር ጦር እየተደረገ ያለው ድጋፍ ለሠራዊቱ ታላቅ አቅም እና ብርታት ፈጥሯል፡፡

በወሎ ግንባር አሸባሪውን የህወሓት ቡድን ለመደምሰስ እየተደረገ ባለው ውጊያ ጥምር ጦሩ እየተፋለመ መሆኑን ገልጸው÷ በግንባሩ ለተሰለፈው ጦር ከደጀኑ ሕዝብ እየተደረገ ያለው ድጋፍ በጀግንነቱ ለሚታወቀው የመከላከያ ሠራዊት ተጨማሪ ብርታት እንደሰጠው ተናግረዋል።

ኢትዮጵያውያን በግንባሩ ለተሰለፈው ሠራዊት እያደረጉ ያሉትን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

አዲሱ ዓመት ኢትዮጵያ የምታሸንፍበት እንዲሆን ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እና ለመከላከያ ሠራዊቱ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

በለይኩን ዓለም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.