ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ የፊፋ የቴክኒክ ባለሙያ ሆነው ተሾሙ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የባህርዳር ከነማ አሰልጣኝ ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ የፊፋ የቴክኒክ ባለሙያ ሆነው ተሾመዋል።
አሰልጣኙ ፊፋ ለቴክኒክ ባለሙያነት ያቀረባቸውን መመዘኛዎች በማለፍ እንደ ሁኔታው በሚታደስ የሁለት ዓመት ኮንትራት የፊፋ የቴክኒክ ባለሙያ ሆነዋል።
ኢንስትራክተር አብርሃም በአፍሪካ ከፍተኛ ኢንስትራክተርነት ፣ በአፍሪካ ዋንጫ እና መሰል ትላልቅ ውድድሮች በቴክኒክ ጥናት ቡድን አባልነት እና አሰልጣኝ በመሆን አገልግለዋል፡፡
በተጨማሪም አሰልጣኙ በእስያ እና የመን እግር ኳስ ላይ ያላቸው የስራ ልምድ ለቦታው ተመራጭ ያደረጋቸው መሆኑን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡