Fana: At a Speed of Life!

የቻን ውድድር የምድብ ድልድል መስከረም 21 ቀን ይፋ ይሆናል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የምትሳተፍበት የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን (ቻን) ውድድር መስከረም 21 ቀን 2015 ዓ.ም ይፋ ይሆናል፡፡

በ2023 በአልጄሪ አስተናጋጅነት በሚከናወነው የቻን ውድድር ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳታፊዎችን ቁጥር ያደገ ሲሆን በ18 ብሔራዊ ቡድኖች መካከል ከጥር 5 እስከ ጥር 27 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ይከናወናል፡፡

በየቀጠናው በተከናወኑ የማጣሪያ ውድድሮች ሞሮኮ፣ ሊቢያ፣ ሴኔጋል፣ ሞሪታኒያ፣ ማሊ፣ ኒጀር፣ ጋና፣ አይቮሪኮስት፣ ኮንጎ፣ ዴሞከራቲክ  ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ካሜሩን፣ ሱዳን፣ ኢትዮጵያ፣ ዩጋንዳ፣ ማዳጋስካር፣ አንጎላ እና ሞዛምቢክ ለውድድሩ አልፈዋል፡፡

ያለፉ ሀገራትም  ከአስተናጋጇ ሀገር አልጄሪያ ጋር በመሆን ውድድራቸውን ለማድረግ እየተጠባበቁ ይገኛሉ።

በመሆኑም ጥር ላይ ለሚጀምረው የውድድር መርሐ ግብር መስከረም 21 ቀን 2015 ዓ.ም በአልጄሪያ ርዕሰ መዲና አልጀርስ የምድብ ድልድል የሚወጣ መሆኑን ከካፍ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በአሠልጣኝ ውበቱ አባተ የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በማጣሪያ ጨዋታዎች የደቡብ ሱዳን እና ሩዋንዳ አቻውን ገጥሞ አንድም ግብ ሳያስተናግድ በተቃራኒው 6 ግቦችን አስቆጥሮ ወደ መድረኩ ከ2016 በኋላ የተመለሰበትን ውጤት ማግኘቱ ይታወሳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.