ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የኳታር ኢንቨስትመንት ባለሥልጣን ኃላፊን ተቀብለው አነጋገሩ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ በኳታር ኢንቨስትመንት ባለሥልጣን የኤዥያ-ፓሲፊክ እና የአፍሪካ ኢንቨስትመንት ኃላፊ ከሆኑት ሼክ ፋይሰል ቢን ታኒ አል-ታኒን ጋር ተወያዩ፡፡
ውይይታቸውም ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የሙዓለ ንዋይ ፍሰት ዕድሎችን በመቃኘት እና በማስፋፋት ላይ ያተኮረ እንደነበር ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።