Fana: At a Speed of Life!

ሚኒስቴሩ የከተሞች የቤት አቅርቦት ወደ 84 ከመቶ ለማሳደግ እየሰራሁ ነው አለ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የከተሞች የቤት አቅርቦት ከ64 ከመቶ ወደ 84 ከመቶ ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን የከተማ ልማትና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

የከተማ ልማትና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ዲኤታ ሔለን ደበበ፥ መንግሥት ባለፉት ዓመታት የቤት ችግሩን ለመቅረፍ ጥረት ሲያደርግ ቢቆይም አሁንም በርካታ ስራዎች እንደሚጠበቅበት ገልጸዋል።

ሚኒስተር ዲኤታዋ ይህን ያሉት የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከደቡብ አፍሪካው ዊትዋተርስራንድ ዪኒቨርስቲ ጋር የሰሩት የወጣቶች ኑሮ ፣ የስራ ዕድል ሁኔታ፣ የመኖሪያ ቤት ጉዳዮችና ትስስሮች ምርምር ይፋ በተደረገበት መድረክ ነው፡፡

በከተሞች የቤት ግንባታ ላይ ብዙ ወጣቶች ተሳታፊ ቢሆኑም እነርሱን ባለቤት ማድረግ ገና ብዙ ስራ እንደሚፈልግ ነው የተናገሩት፡፡

ሚኒስቴሩ በቀጣዮቹ አስር ዓመታትም ከግል ተቋማት ፣ ዩኒቨርስቲዎች፣ ከአጋር ተቋማትና ምርምር ተቋማት ጋር በጋራ ይሰራል ብለዋል፡፡

ሚኒስትር ዴኤታዋ አክለውም ፥ አሁን ላይ ያለውን 64 በመቶ የከተሞች የቤት ሽፋን ወደ 84 በመቶ ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን ነው የገለጹት።

ከመድረኩ የሚገኘውን ሀሳብ በመከለስ ለፖሊሲ ግብዓት እንደሚገለገልበት ገልፀዋል።

የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ ፥ ዪኒቨርስቲው ለሚሰራው ስራና የመኖሪያ ቤት ትስስር የምርምር ስራ ከተማ አስተዳደሩ ከጎኑ መሆኑን ነው የተናሩት።

የሐዋሳ ዩኒቨርሰቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አያኖ በራሶ ፥ የምርምር ፕሮጀክቱ ዩኒቨርሲቲው ከውጪ ሀገር ተቋማት ጋር ከሚያካሔዳቸው 71 የትብብር ፕሮጀክቶች ውስጥ አንዱ የሆነው ከሼፊልድና ዌትስ ዪኒቨርስቲዎች ጋር በጋራ የሚያከናውነው ‘‘ዩዝ ፊውቸር’’ የተሰኘ የምርምር ፕሮጀክት ነው ብለዋል።

በመድረኩ ላይ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዲኤታ ዶ/ር በከር ሻሌን ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

በመቅደስ አስፋው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.